ማሳሰቢያ፤ እርዳታ በሚያደርጉበት ጊዜ ቲፕ መክፈል አይኖርብዎትም። ጎፈንድሚ ሰርቪስ ከሚለው ስር የሚያዩትን አስራ ሁለት ነጥብ አምስት ፐርሰንት የሚለውን ወደ ዜሮ ፐርሰንት መቀየር ይኖርብዎታል።
===================================================
አሸባሪ የጥፋት ኃይሎች እና ግብረ አበሮቻቸው በከፈቱት ጦርነት ምክንያት በተለይ በአማራ እና አፋር ክልል የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን የጦርነት ሰለባ እየሆኑ፣ ሰብዓዊ መብታቸው እየተረገጠ፣ ሃብታቸው እና ንብረታቸው እየወደመ፣ የዕለት ጉርሳቸው ሳይቀር እየተዘረፈ፣ አሰቃቂ ወንጀል እና ጅምላ ጭፍጨፋ እየተፈጸመባቸው ሲሆን አገራችን ኢትዮጵያም በውስጥም በውጭም በሚደርስባት ጫና የሕልውና አደጋ ተደቅኖባት በከባድ እና ታሪካዊ ፈተና ዉስጥ ትገኛለች፡፡ ወገኖቻችን ተገደው በገቡበት ጦርነት ምክንያት ውድ እና ክቡር የሆነውን ህይወታቸውን እየሰዉ እና የአካል ጉዳት እየደረሰባቸው ሲሆን ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰላማዊ ዜጎች ደግሞ ከቀያቸው ተፈናቅለው ያለ መጠለያ እና ምግብ፣ በረሃብ፣ በበሽታ እና